መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ታኅሣሥ 2016

ይህ እትም ከጥር 30 እስከ የካቲት 26, 2017 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

የሕይወት ታሪክ

“ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ሁሉንም ነገር” መሆን

ዴንተን ሆፕኪንሰን ከወጣትነቱ ጀምሮ የተሰጡት በርካታ ኃላፊነቶች ይሖዋ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች እንደሚወድ ለመገንዘብ አስችሎታል።

በጸጋው ነፃ ወጥታችኋል

ይሖዋ ከኃጢአት ነፃ ያወጣህ እንዴት እንደሆነ ማንበብህ በእጅጉ ይጠቅምሃል።

‘በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ሕይወትና ሰላም ያስገኛል’

ሮም ምዕራፍ 8 ይሖዋ ለሰው ዘር በሙሉ ያዘጋጀውን ሽልማት ለማግኘት የሚረዳን ምክር ይዞልናል።

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በደንብ አንብበሃቸዋል? እስቲ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር።

የሚያስጨንቃችሁን ነገር ሁሉ በይሖዋ ላይ ጣሉ

የአምላክ አገልጋዮችም ጭንቀት ሊሰማቸው ይችላል። ‘የአምላክን ሰላም’ ለማግኘት የሚረዱ አራት ጠቃሚ እርምጃዎች አሉ።

ይሖዋ ከልብ ለሚፈልጉት ወሮታ ከፋይ ነው

ይሖዋ ወሮታ እንደሚከፍለን የሰጠን ተስፋ የሚጠቅመን እንዴት ነው? ይሖዋ ቀደም ባሉት ዘመናት ለአገልጋዮቹ ወሮታ የከፈላቸው እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜስ ይህን እያደረገ ያለው እንዴት ነው?

ገርነት—ጥበብ የሚንጸባረቅበት ጎዳና

ሰዎች ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲያደርጉብን ስሜታችንን መቆጣጠር ቀላል አይደለም፤ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ገርነት እንድናሳይ እንድንሆን ያበረታታናል። ታዲያ ይህን መልካም ባሕርይ ለማዳበር ምን ይረዳናል?

የ2016 መጠበቂያ ግንብ ርዕስ ማውጫ

ለሕዝብ በሚሰራጨውና በጥናት እትሞች ላይ የወጡ ርዕሰ ጉዳዮች ዝርዝር።