መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥር 2017

ይህ እትም ከየካቲት 27 እስከ ሚያዝያ 2, 2017 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል

ወደ ሌላ አገር ተዛውረው ያገለገሉ በርካታ እህቶች መጀመሪያ ላይ ይህን ውሳኔ ለማድረግ ፈራ ተባ ብለው ነበር። ታዲያ ድፍረት ያገኙት እንዴት ነው? በውጭ አገር በአገልግሎት ካሳለፏቸው ዓመታትስ ምን ትምህርት አግኝተዋል?

“በይሖዋ ታመን፤ መልካም የሆነውንም አድርግ”

ይሖዋ፣ ራሳችን ማድረግ የማንችለውን ነገር ለእኛ ሊያደርግልን ይፈልጋል። ሆኖም እኛም አቅማችን የሚፈቀደውን እንድናደርግ ይጠብቅብናል። የ2017 የዓመት ጥቅሳችን በዚህ ረገድ የሚረዳን እንዴት ነው?

የመምረጥ ነፃነታችሁን ታደንቃላችሁ?

የመምረጥ ነፃነት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስስ ስለዚህ ውድ ስጦታ ምን ያስተምራል? የሌሎችን የመምረጥ ነፃነት እንደምታከብር ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ልክን ማወቅ ዛሬም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ልክን ማወቅ ምንድን ነው? ከትሕትና ጋር የሚዛመደው እንዴት ነው? ልናዳብረው የሚገባ ግሩም ባሕርይ የሆነውስ ለምንድን ነው?

ተፈታታኝ ሁኔታ በሚያጋጥመን ጊዜም ልካችንን ማወቅ

ያለንበት ሁኔታ በሚቀየርበት፣ ትችት በሚሰነዘርብን ወይም አድናቆት በሚቸረን እንዲሁም ውሳኔያችን የሚያስከትለውን ውጤት በማናውቅበት ጊዜም እንኳ ልካችንን ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?

እነዚህን ነገሮች “ታማኝ ለሆኑ ሰዎች አደራ ስጥ”

በዕድሜ የገፉ ወንድሞች ወጣቶች ተጨማሪ ኃላፊነት እንዲሸከሙ ማሰልጠን የሚችሉት እንዴት ነው? ወጣቶችስ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ ለነበሩ ወንድሞች አድናቆት እንዳላቸው ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሰዎች እሳትን ከቦታ ወደ ቦታ የሚያጓጉዙት እንዴት ነበር?