በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዓለም በተቃወሰበት ጊዜ

1 | ጤንነትህ

1 | ጤንነትህ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

አንድ ዓይነት ቀውስ ወይም አደጋ ሲከሰት በሰዎች ጤና ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም።

  • ችግሮች በሰዎች ላይ ውጥረት ይፈጥራሉ፤ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ጭንቀት ደግሞ ለበሽታ ያጋልጣቸዋል።

  • ትላልቅ ችግሮች በጤና ተቋማት ላይ ጫና ይፈጥራሉ፤ በቂ የሕክምና ግብአቶች ማግኘትም አስቸጋሪ ይሆናል።

  • አደጋዎች የሰዎችን ኪስ ይጎዳሉ፤ ይህም የተመጣጠነ ምግብ ወይም ጥሩ ሕክምና ለማግኘት አቅም እንዳይኖራቸው ያደርጋል።

ማወቅ ያለብህ ነገር

  • ከባድ የጤና እክልና ጭንቀት አስተሳሰብህን ሊያዛባው ይችላል፤ ይህ ደግሞ ጤንነትህን ለመጠበቅ የሚረዱህን ልማዶች ችላ እንድትል ያደርግሃል። በመሆኑም የጤንነትህ ሁኔታ የባሰ እየከፋ ይሄዳል።

  • አስፈላጊውን ሕክምና ካላገኘህ ያሉብህ የጤና ችግሮች እየተባባሱ ሊሄዱ ይችላሉ፤ አልፎም ለሕይወት የሚያሰጋ ደረጃ ላይ ይደርሱ ይሆናል።

  • ጤናማ ከሆንክ ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የተሻለ አቅም ይኖርሃል።

  • የኑሮ ደረጃህ ምንም ይሁን ምን ጤናህን ለመጠበቅ ማድረግ የምትችላቸው ነገሮች አሉ።

አሁን ማድረግ የምትችለው ነገር

ጥበበኛ ሰው ሊያጋጥሙት የሚችሉ አደጋዎችን አርቆ ያስባል፤ የሚቻል ከሆነም፣ ራሱን ከአደጋዎች ለመጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል። ይህ ከጤና ጋር በተያያዘም እውነት ነው። ንጽሕናን መጠበቅ የበሽታ ተጋላጭነትን ይቀንሳል፤ ወይም በሽታው የከፋ እንዳይሆን ያደርጋል። ታምሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ እንደሚባለው ነው።

“የራሳችንንም ሆነ የቤታችንን ንጽሕና መጠበቃችን በኋላ ላይ ለሕክምናም ሆነ ለመድኃኒት የሚያስፈልገንን ወጪ እንደሚቀንስልን ምንም ጥያቄ የለውም።”—አንድርያስ *

^ በዚህ መጽሔት ላይ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።