በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የገንዘብ አያያዝ

የገንዘብ አያያዝ

ብዙ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች በመከተላቸው ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥማቸውን ችግር መቀነስ ችለዋል።

ዕቅድ አውጣ

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “የትጉ ሰው ዕቅድ ለስኬት ያበቃዋል፤ ችኩሎች ሁሉ ግን ለድህነት ይዳረጋሉ።”—ምሳሌ 21:5

ምን ማለት ነው? ባወጣኸው ዕቅድ መመራትህ ገንዘብህን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችልሃል። ስለዚህ ያለዕቅድ ገንዘብ አታውጣ። የምትፈልገውን ነገር ሁሉ መግዛት እንደማትችል በማስታወስ ገንዘብህን በአግባቡ ተጠቀምበት።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

  • በጀት አውጣ። ወጪዎችህን በዝርዝር ጻፍ፤ ከዚያም በየፈርጁ መድባቸው። ቀጥሎም ለእያንዳንዱ ፈርጅ ገንዘብ መድብ። ለአንድ ጉዳይ ከመደብከው በላይ ገንዘብ ካወጣህ ከሌላ ፈርጅ ወስደህ አካክስ። ለምሳሌ ነዳጅ ለመቅዳት ካቀድከው በላይ ገንዘብ ካወጣህ እምብዛም አስፈላጊ ላልሆነ ነገር ምናልባትም ውጭ ለመብላት ከመደብከው ገንዘብ ወስደህ አካክስ።

  • አላስፈላጊ ዕዳ ውስጥ አትግባ። በተቻለ መጠን ዕዳ ውስጥ ላለመግባት ጥረት አድርግ። ከዚህ ይልቅ የምትፈልገውን ነገር ለመግዛት ገንዘብ አጠራቅም። ክሬዲት ካርድ የምትጠቀም ወይም በዱቤ የምትገዛ ከሆነ ወለድ እንዳትጠየቅ በየወሩ ሙሉውን ክፍያ አጠናቅቅ። ዕዳ ካለብህ ዕዳህን ለመክፈል የሚያስችል ዕቅድ አውጣ፤ ከዚያም በዕቅድህ መሠረት ክፈል።

    አንድ ጥናት እንደገለጸው ክሬዲት ካርድ የሚጠቀሙ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ብዙ ገንዘብ ያወጣሉ። ስለዚህ ክሬዲት ካርድ ካለህ በጥንቃቄ ተጠቀምበት።

ጎጂ ዝንባሌዎችን አስወግድ

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ሰነፍ ሰው በክረምት አያርስም፤ በመሆኑም በመከር ወራት ባዶውን ሲቀር ይለምናል።”—ምሳሌ 20:4

ምን ማለት ነው? ስንፍና ለድህነት ሊዳርግ ይችላል። ስለዚህ ትጉ ሠራተኛ ሁን፤ እንዲሁም በቻልከው መጠን ለወደፊት የሚሆን ገንዘብ አጠራቅም።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

  • ታታሪ ሁን። የገቢ ምንጭህን እንዳታጣ ሥራህን በትጋት አከናውን፤ እንዲሁም እምነት የሚጣልብህ ሁን። አሠሪዎች ታታሪ ሠራተኛ ይፈልጋሉ።

  • ሐቀኛ ሁን። የመሥሪያ ቤትህን ንብረት አትስረቅ። ሐቀኝነት ማጉደልህ መልካም ስምህን ሊያጎድፍና ወደፊት ሌላ ሥራ ማግኘት ከባድ እንዲሆንብህ ሊያደርግ ይችላል።

  • ስግብግብ አትሁን። ለገንዘብ ሚዛናዊ ያልሆነ አመለካከት ካለህ ጤንነትህም ሆነ ከሌሎች ጋር ያለህ ግንኙነት ሊበላሽ ይችላል። በሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር ገንዘብ እንዳልሆነ አስታውስ።

ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች

መጽሐፍ ቅዱስን ኢንተርኔት ላይ አንብብ፤ jw.org ላይ በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ይገኛል

በመጥፎ ልማዶች የተነሳ ጊዜና ገንዘብ አታባክን።

“ሰካራምና ሆዳም ይደኸያሉና፤ ድብታ ሰውን የተቦጫጨቀ ልብስ ያስለብሰዋል።”​—ምሳሌ 23:21

ከመጠን በላይ አትጨነቅ።

“ስለዚህ እላችኋለሁ፦ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንበላለን፣ ምንስ እንጠጣለን ወይም ደግሞ ስለ ሰውነታችሁ ምን እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ።”​—ማቴዎስ 6:25

አትቅና።

“ቀናተኛ ሰው ሀብት ለማግኘት ይጓጓል፤ ድህነት ላይ እንደሚወድቅ አያውቅም።”​—ምሳሌ 28:22