በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የተሳሳተ ትምህርት 1፦ ነፍስ አትሞትም

የተሳሳተ ትምህርት 1፦ ነፍስ አትሞትም

ይህ የተሳሳተ ትምህርት የመነጨው ከየት ነው?

“የጥንቶቹ የክርስትና ፈላስፎች፣ ነፍስ አትሞትም የሚለውን የግሪክ ጽንሰ ሐሳብ እንዲሁም አምላክ ነፍስን ከፈጠረ በኋላ አንድ ሰው በሚፀነስበት ጊዜ ወደ አካሉ ያስገባታል የሚለውን ትምህርት ተቀብለው ነበር።”—ዘ ኒው ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ (1988)፣ ጥራዝ 11፣ ገጽ 25

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።”—ሕዝቅኤል 18:4

መጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያውን ሰው አፈጣጠር በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ [በዕብራይስጥ፣ ነፈሽ] ሆነ።”—ዘፍጥረት 2:7

“ነፍስ” ተብሎ የተተረጎመው ነፈሽ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ‘የሚተነፍስ ፍጡር’ የሚል ፍቺ አለው። አምላክ የመጀመሪያውን ሰው አዳምን ሲፈጥረው ወደ አካሉ ያስገባው ሕይወቱን የሚያቆይ ኃይል እንጂ የማትሞት ነፍስ አይደለም፤ ይህ የሕይወት ኃይል በሰውነቱ ውስጥ እንዲቆይ አዳም መተንፈስ ነበረበት። ከዚህ አንጻር “ነፍስ” በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚያመለክተው የአንድን ሰው የተወሰነ ክፍል ሳይሆን በሕይወት ያለውን ግለሰብ እንዳለ ነው። አምላክ መጀመሪያ ለሰው የሰጠው ሕይወትን የሚያቆይ ኃይል ከሰው ከወጣ ነፍስ ማለትም ሰውየው ይሞታል።—ዘፍጥረት 3:19፤ ሕዝቅኤል 18:20

ነፍስ አትሞትም የሚለው መሠረተ ትምህርት የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስነስቷል፦ ከሞት በኋላ ነፍስ ወዴት ትሄዳለች? የክፉዎች ነፍስ ምን ይሆናል? ስመ ክርስትና፣ ነፍስ አትሞትም የሚለውን የተሳሳተ ትምህርት መቀበሏ ሌላ የተሳሳተ ትምህርት ይኸውም የመቃጠያ እሳት አለ የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ወደ መቀበል መርቷታል።

እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አወዳድር፦ መክብብ 3:19፤ ማቴዎስ 10:28፤ የሐዋርያት ሥራ 3:23

እውነታው፦

አንድ ሰው ሲሞት ከሕልውና ውጪ ይሆናል