በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ትዳርን አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ትዳርን አስደሳች ማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ የሚሰጠው ምክር ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም ይህን ምክር ያስጻፈው የጋብቻ መሥራች የሆነው ይሖዋ አምላክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ትዳርን አስደሳች ለማደረግ የሚረዱ ባሕርያትን እንድናዳብር ያስተምረናል፤ ትዳርን ሊያናጉ የሚችሉ ዝንባሌዎችንም እንድናስወግድ ያስጠነቅቀናል። በተጨማሪም በትዳር ውስጥ ደስታ እንዲሰፍን በምን መንገድ የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ እንዳለብን ያስተምረናል።—ቆላስይስ 3:8-10, 12-14ን አንብብ።

ባልና ሚስት እርስ በርስ መከባበር ይኖርባቸዋል። ሁለቱም፣ በትዳር ውስጥ የሚኖራቸውን ድርሻ በተመለከተ አምላክ የሰጠውን መመሪያ የሚጠብቁ ከሆነ ደስተኛ መሆን ይችላሉ።—ቆላስይስ 3:18, 19ን አንብብ።

ትዳርን ዘላቂ የሚያደርገው ምንድን ነው?

የተጋቡ ሰዎች፣ ትዳራቸው ዘላቂ የሚሆነው እርስ በርስ የሚዋደዱ ከሆነ ነው። አምላክ፣ ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል። እሱና ልጁ ኢየሱስ፣ የራስን ጥቅም መሥዋዕት በማድረግ ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ግሩም ምሳሌ ይሆኑናል።—1 ዮሐንስ 4:7, 8, 19ን አንብብ።

ባልና ሚስት፣ ትዳርን የአምላክ ዝግጅት እንደሆነ አድርገው በመመልከት የሚያከብሩት ከሆነ ትዳራቸው ዘላቂ እንዲሆን ለማድረግ ይጥራሉ። አምላክ ጋብቻን ያቋቋመው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ዘላቂ ጥምረት እንዲፈጠር በማሰብ ነው፤ ይህም ቤተሰቦች ጥበቃ እንዲያገኙና የደኅንነት ስሜት እንዲኖራቸው ያደርጋል። አምላክ ወንዶችንና ሴቶችን የፈጠረው አንዳቸው የሌላውን አካላዊ እና ስሜታዊ ፍላጎት ማሟላት እንዲችሉ አድርጎ መሆኑ ትዳር ዘላቂ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል። በተጨማሪም ሰዎችን የፈጠራቸው በራሱ መልክ ይኸውም እንደ እሱ፣ ፍቅር የማሳየት ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጎ ነው።—ዘፍጥረት 1:27ን እና 2:18, 24ን አንብብ።