በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 94

ለአምላክ ቃል አመስጋኝ መሆን

ለአምላክ ቃል አመስጋኝ መሆን

(ፊልጵስዩስ 2:16)

  1. 1. ይሖዋ አባት ሆይ፣ ደርሶናል ቃልህ፤

    ማመስገን እንሻለን ለስጦታህ።

    በመንፈስህ በመምራት

    አ’ጻፍክ ሐሳብህን፤

    ቃልህ ብርሃን ሆነን፤ እውነትን ተማርን።

  2. 2. ወደ ልብ ይዘልቃል፤ ቃልህ አለው ኃይል፤

    መንፈስንና ነፍስን ይለያያል።

    እንከን የለውም ሕግህ፤

    ፍጹም ነው ት’ዛዝህ፤

    አስተማማኝ ናቸው መመሪያዎችህ።

  3. 3. በሰዎች ተጠቅመህ ባ’ጻፍከው ቃልህ

    ልባችን ተነካ፤ አንተን አወቅንህ።

    ቃልህን ሰጥተኸናል፤

    ይድረስህ ምስጋና፤

    እምነታችን ይደግ፣ ይሁን ጠንካራ።

(በተጨማሪም መዝ. 19:9⁠፤ 119:16, 162⁠ን፣ 2 ጢሞ. 3:16⁠ን፣ ያዕ. 5:17⁠ን እና 2 ጴጥ. 1:21⁠ን ተመልከት።)