በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 98

ቅዱሳን መጻሕፍት በመንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው

ቅዱሳን መጻሕፍት በመንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው

(2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17)

  1. 1. ያምላክ ቃል ነው ብርሃናችን፤

    መብራት ለመንገዳችን።

    ዘወትር ብንከተለው፣

    ነፃ ያወጣል እውነት ነው።

  2. 2. በአምላክ መንፈስ ተጽፏል፤

    ሕጉን ያስተምረናል።

    ለሥራ ያነሳሳናል፤

    ተግሣጽ፣ ምክር ይሰጠናል።

  3. 3. አምላክ በሰጠን በዚህ ቃል፣

    የሱን ፍቅር አውቀናል።

    ካነበብነው በየ’ለቱ

    ይመራናል በመንገዱ።

(በተጨማሪም መዝ. 119:105⁠ን እና ምሳሌ 4:13⁠ን ተመልከት።)