በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ilbusca/E+ via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ሰዎች በሰላም መኖር ያቃታቸው ለምን ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሰዎች በሰላም መኖር ያቃታቸው ለምን ይሆን?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 የዓለም መሪዎችና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች ሰላም ማስፈን አልቻሉም። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ግጭቶች ይህን ያህል የበዙበት ጊዜ የለም። የዓለም ሕዝብ አንድ አራተኛው ማለትም ሁለት ቢሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎች የሚኖሩት እንዲህ ያሉ ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ነው።

 የሰው ልጆች ሰላም ማምጣት ያልቻሉት ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የሰው ልጆች ሰላም ማስፈን የማይችሉባቸው ሦስት ምክንያቶች

  1.  1. ሰዎች የሚያንጸባርቋቸው ባሕርያት ሰላም ለማስፈን ጥረት እንኳ እንዳያደርጉ እንቅፋት ይሆኑባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናችን የሚኖሩ ሰዎች ምን ዓይነት ባሕርይ እንደሚኖራቸው አስቀድሞ ተናግሯል፤ እንዲህ ይላል፦ “ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ ጉረኞች፣ ትዕቢተኞች፣ . . . ታማኝ ያልሆኑ፣ . . . ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ፣ . . . ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ . . . ግትሮች፣ በኩራት የተወጠሩ . . . ይሆናሉ።”—2 ጢሞቴዎስ 3:2-4

  2.  2. የሰው ልጆች የፈጣሪያቸው የይሖዋ a አምላክ እርዳታ እስካልተጨመረበት ድረስ በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ ችግሮቻቸውን ለመፍታት አቅሙ የላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ “[ሰው] አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም” በማለት በግልጽ ይናገራል።—ኤርምያስ 10:23

  3.  3. ዓለም፣ ሰይጣን ዲያብሎስ በተባለ ኃያልና ጨካኝ ገዢ ተጽዕኖ ሥር ሲሆን ይህ ገዢ “መላውን ዓለም እያሳሳተ” ነው። (ራእይ 12:9) “መላው ዓለም . . . በክፉው ቁጥጥር ሥር” እስከሆነ ድረስ ጦርነትና ግጭት መኖሩ አይቀሬ ነው።—1 ዮሐንስ 5:19

ሰላም ማስፈን የሚችለው ማን ነው?

 መጽሐፍ ቅዱስ በሰዎች ጥረት ሳይሆን በአምላክ ጣልቃ ገብነት ሰላም እንደሚሰፍን ማረጋገጫ ይሰጠናል።

  •   “‘ለእናንተ የማስበውን ሐሳብ በሚገባ አውቀዋለሁና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ የማስበው ጥፋትን ሳይሆን ሰላምን እንዲሁም የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን ነው።’”—ኤርምያስ 29:11

 አምላክ፣ የገባውን ይህን ቃል የሚፈጽመው እንዴት ነው? ‘ሰላም የሚሰጠው አምላክ ሰይጣንን ይጨፈልቀዋል።’ (ሮም 16:20) አምላክ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ‘የአምላክ መንግሥት’ ተብሎ የተገለጸውን መስተዳድር በመጠቀም በመላዋ ምድር ላይ ሰላም ያሰፍናል። (ሉቃስ 4:43) የዚህ መንግሥት ንጉሥ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አገዛዝ ሥር ሰዎች በሰላም መኖር የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ይማራሉ።—ኢሳይያስ 9:6, 7

a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18