በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ናዴዥዳ ኮሮቦችኮ፣ ወንድም ኢጎር ክሌትኪን እና ወንድም ኒኮላይ ኮኖኔንኮ

ሚያዝያ 1, 2024
ሩሲያ

“እጅ መስጠት አማራጭ አይደለም”

“እጅ መስጠት አማራጭ አይደለም”

በካባሮቭስክ ግዛት የሚገኘው የኒኮላዬቭስክ ኦን አሙር ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ኢጎር ክሌትኪን፣ በወንድም ኒኮላይ ኮኖኔንኮ እና በእህት ናዴዥዳ ኮሮቦችኮ ክስ ላይ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ የሚታመኑበትን እና “አንተ አምላኬ ነህ” የሚሉትን ሁሉ በፍቅር ስለሚንከባከብና ስለሚደግፋቸው እናመሰግነዋለን።​—መዝሙር 31:14

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 11, 2021

    የኢጎር እና የናዴዥዳ ቤቶች ተፈተሹ። ኢጎር ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ

  2. ጥቅምት 12, 2021

    ናዴዥዳ ምርመራ ተደረገባት

  3. ጥቅምት 13, 2021

    ኢጎር ከጣቢያ ተለቀቀ

  4. ጥቅምት 14, 2021

    ኢጎር እና ናዴዥዳ የጉዞ ገደቦች ተጣሉባቸው

  5. መስከረም 27, 2022

    ኒኮላይ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  6. ጥር 16, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ