በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዩሪ ዩስኮቭ

መጋቢት 22, 2024
ሩሲያ

የ85 ዓመቱ ወንድም ዩሪ ዩስኮቭ ጥፋተኛ ተባለ

የ85 ዓመቱ ወንድም ዩሪ ዩስኮቭ ጥፋተኛ ተባለ

መጋቢት 15, 2024 በቹቫሽ ሪፑብሊክ የሚገኘው የኖቮቼቦክሳርስክ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ዩሪ ዩስኮቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ የአምስት ዓመት የገደብ እስራት በይኖበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

አጭር መግለጫ

እንደ ዩሪ ያሉ በዕድሜ የገፉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ለሚያሳዩት ግሩም የታማኝነትና የጽናት ምሳሌ አመስጋኝ ነን። ይሖዋ ፈጽሞ እንደማይጥላቸው እንዲሁም ለእነሱ ሲል ኃያልነቱን እንደሚያሳይ እናውቃለን።​—መዝሙር 71:18, 19

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 4, 2023

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  2. ግንቦት 5, 2023

    ቤቱ ተፈተሸ። የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  3. ጥር 23, 2024

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  4. መጋቢት 15, 2024

    ጥፋተኛ ተብሎ የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደበት

a ወንድም ዩሪ አስተያየት የሰጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ ከመስማቱ በፊት ነው።