በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የመጽሐፍ ቅዱስ ፍሬ ሐሳብ

የመጽሐፍ ቅዱስ ፍሬ ሐሳብ

መጽሐፍ ቅዱስ በታሪክ ዘመናት ሁሉ በስፋት በመሰራጨት ረገድ ወደር የሌለው መጽሐፍ ነው፤ ብዙዎች ይህን መጽሐፍ ይወዱታል። ይሁን እንጂ ‘ይህ ታዋቂ መጽሐፍ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?’ ብለህ ታስብ ይሆናል።

መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር የመጽሐፍ ቅዱስን ፍሬ ሐሳብ ይዟል፤ ይህ ብሮሹር የመጽሐፍ ቅዱስን አጠቃላይ መልእክት ለመረዳት ያስችላል። ብሮሹሩ በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኘው የፍጥረት ዘገባ አንስቶ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ እስከሚገኘው አስደናቂ ተስፋ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት በአጭሩ ይዳስሳል። ይህ ብሮሹር ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ክንውኖች የተፈጸሙበትን ጊዜ የሚያሳይ የጊዜ ሰሌዳ ይዟል። በተጨማሪም ማራኪ የሆኑ ሥዕሎችንና ለውይይት የሚሆኑ አመራማሪ ጥያቄዎችን አካትቷል።

መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ኢንተርኔት ላይ አንብብ።