በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንጽሔ ይናገራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንጽሔ ይናገራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 አይናገርም። “መንጽሔ” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ አይገኝም፤ በተጨማሪም የሞቱ ሰዎች ነፍስ በመንጽሔ እንደሚነጻ አያስተምርም። a መጽሐፍ ቅዱስ ሞትንና ሕይወትን አስመልክቶ ምን እንደሚያስተምርና ይህም ከመንጽሔ ትምህርት የተለየ የሆነው እንዴት እንደሆነ እንመልከት።

  •   አንድን ሰው ከኃጢአት የሚያነጻው በኢየሱስ ደም ላይ ያለው እምነት እንጂ መንጽሔ ተብሎ በሚጠራ ቦታ የሚያሳልፈው ጊዜ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ “የልጁ [የአምላክ ልጅ] የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” ይላል። በተጨማሪም ‘ኢየሱስ ክርስቶስ በገዛ ደሙ አማካኝነት ከኃጢአታችን ነፃ አውጥቶናል’ በማለት ይናገራል። (1 ዮሐንስ 1:7፤ ራእይ 1:5) ኢየሱስ “በብዙ ሰዎች ምትክ ሕይወቱን ቤዛ” አድርጎ በመስጠት የኃጢአታቸውን ዋጋ ከፍሏል።—ማቴዎስ 20:28

  •   የሞቱ ሰዎች ምንም ነገር አያውቁም። “ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም።” (መክብብ 9:5) የሞተ ሰው ምንም ዓይነት ስሜት ስለሌለው በመንጽሔ እሳት ሊነጻ አይችልም።

  •   አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ለኃጢአቱ አይቀጣም። መጽሐፍ ቅዱስ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው” እንዲሁም “የሞተ ከኃጢአቱ ነፃ ወጥቷል” በማለት ይናገራል። (ሮም 6:7, 23) ሞት ለኃጢአት ተመጣጣኝና የተሟላ ቅጣት ነው።

a ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒድያ ሁለተኛ እትም ገጽ 824ን ተመልከት።

b ኦርፊየስ ኤ ጀነራል ሂስትሪ ኦፍ ሪልጅን የተባለው መጽሐፍ ስለ መንጽሔ ሲናገር “በወንጌሎች ውስጥ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገር አንድ ቃል እንኳ አይገኝም” ብሏል። በተመሳሳይም ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒድያ “በአጠቃላይ፣ ካቶሊክ ስለ መንጽሔ የምታስተምረው ትምህርት በቅዱሳን ጽሑፎች ላይ ሳይሆን በወግ ላይ የተመሠረተው ነው” ይላል።—ሁለተኛ እትም ጥራዝ 11 ገጽ 825