በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች አሥራት ይሰጣሉ?

የይሖዋ ምሥክሮች አሥራት ይሰጣሉ?

 የይሖዋ ምሥክሮች አሥራት አይሰጡም፤ ሥራችን ድጋፍ የሚያገኘው ሰዎች በፈቃደኝነት በሚያደርጉት የገንዘብ መዋጮ ነው። ለመሆኑ አሥራት ምንድን ነው? የይሖዋ ምሥክሮች አሥራት የማይሰጡትስ ለምንድን ነው?

 የአሥራት ሕግ ይኸውም አንድ ሰው ከንብረቱ አንድ አሥረኛውን እንዲያዋጣ የሚያዝዘው ደንብ ለጥንቱ የእስራኤል ብሔር የተሰጠው ሕግ ክፍል ነበር። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ‘አሥራት ስለመቀበል የሚያዝዘውን ሕግ’ ጨምሮ የሙሴ ሕግ ለክርስቲያኖች እንደማይሠራ በግልጽ ይናገራል።​—ዕብራውያን 7:5, 18፤ ቆላስይስ 2:13, 14

 የይሖዋ ምሥክሮች የግዳጅ አሥራት ከመስጠት ወይም መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅ የጥንቶቹን ክርስቲያኖች ፈለግ በመከተል ለአገልግሎታቸው ድጋፍ የሚሰጡባቸው ሁለት መንገዶች አሉ፤ እነሱም፦ አንደኛ ምንም ገንዘብ ሳይከፈላቸው፣ በግለሰብ ደረጃ በስብከቱ ሥራ መሳተፍ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በፈቃደኝነት የገንዘብ መዋጮ ማድረግ ናቸው።

 በመሆኑም ለክርስቲያኖች የተሰጠውን የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ እንከተላለን፦ “አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ።”​—2 ቆሮንቶስ 9:7