በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጭፍን ጥላቻን ማሸነፍ

ጭፍን ጥላቻን ማሸነፍ

እኛ የይሖዋ ምሥክሮች የትኛውም ዘር በአምላክ ፊት እኩል እንደሆነ እናምናለን። (የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35) መጽሐፍ ቅዱስን በማስተማር፣ ሰዎች በውስጣቸው ያለውን ሥር የሰደደ ጭፍን ጥላቻ እንዲያስወግዱ እንረዳለን።

በተጨማሪም በዘር ወይም በብሔር ጥላቻ ላይ የተመሠረተን ማንኛውንም እንቅስቃሴ አንደግፍም። ለምሳሌ ያህል፣ በናዚ ዘመን በጀርመንም ሆነ በሌሎች አገሮች የነበሩ የይሖዋ ምሥክሮች ሂትለር በጥላቻ ተነሳስቶ ያካሄደውን ዘመቻ ለመደገፍ ፈቃደኞች አልሆኑም። በዚህ አቋማቸው ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

ከዚህም ሌላ በ1994 በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ይካሄድ በነበረበት ወቅት የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ ዘመቻ አልተሳተፉም። እንዲያውም እየታደኑ ይገደሉ የነበሩትን ሰዎች ለመታደግ ሲሉ ራሳቸውን ለአደጋ ያጋለጡ አልፎ ተርፎም ሕይወታቸውን ያጡ አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች አሉ።

ሁሉንም ሰዎች የመርዳት ፍላጎት ስላለን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን 600 ገደማ በሚሆኑ ቋንቋዎች እናዘጋጃለን እንዲሁም እናሰራጫለን። በውጤቱም ጉባኤዎቻችን “ከሁሉም ብሔራት፣ ነገዶች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች የተውጣጡ” ሰዎችን ያቀፉ ሊሆኑ ችለዋል።—ራእይ 7:9

አደጋ በሚደርስበት ጊዜ ፍቅር እርዳታ ለመስጠት ያነሳሳናል