በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የቤቴል ጉብኝት

ቤቴል በሚል ስያሜ የሚታወቁትን ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን እንድትጎበኝ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልሃለን። በአንዳንዶቹ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ ያለአስጎብኚ የሚታዩ አውደ ርዕዮችም ተዘጋጅተዋል።

ጉብኝት በድጋሚ ተጀምሯል፦ ከሰኔ 1, 2023 አንስቶ በብዙ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችን በድጋሚ ለጉብኝት ክፍት ሆነዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት መጎብኘት የምትፈልገውን ቅርንጫፍ ቢሮ አነጋግር። በኮቪድ-19 መያዝህ በምርመራ ከተረጋገጠ፣ የጉንፋን ምልክት ከታየብህ ወይም በቅርቡ በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ተገናኝተህ ከነበረ እባክህ ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን አትጎብኝ።

ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ

 የጉብኝት መረጃ

የጉብኝት ቀጠሮ አስይዝ—ቁጥራቸው 20 የማይሞላ ሰዎች

የጉብኝት ቀጠሮ አስይዝ—20 ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች

የጉብኝት ቀጠሮህን ተመልከት ወይም ቀይር

የጉብኝት ብሮሹር አውርድ—ዎርዊክ

የጉብኝት ብሮሹር አውርድ—ፓተርሰን

የጉብኝት ብሮሹር አውርድ—ዎልኪል

 አውደ ርዕይ

ያለአስጎብኚ የሚታይ ኤግዚቢሽን—ዎርዊክ

መጽሐፍ ቅዱስ እና መለኮታዊው ስም። ይህ አውደ ርዕይ በቀላሉ የማይገኙ መጽሐፍ ቅዱሶችን እንዲሁም የአምላክን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ሙከራው የከሸፈው እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያስቃኝ ነው። በተጨማሪም አውደ ርዕዩ ሌሎች የጥንት መጽሐፍ ቅዱሶችንና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የተያያዙ ቁሳቁሶችን የሚያሳይ ተሽከርካሪ ሙዚየም ይዟል።

ለይሖዋ ስም የሚሆን ሕዝብ። ይህ አውደ ርዕይ የይሖዋ ምሥክሮችን መንፈሳዊ ቅርስ የሚያሳይ ነው። በዚያ የሚገኙት ቁሳቁሶች፣ ሥዕሎች እና ባለታሪኮቹ የጻፏቸው ዘገባዎች ይሖዋ ሕዝቦቹ ፈቃዱን እንዲፈጽሙ ቀስ በቀስ የመራቸው፣ ያስተማራቸውና ያደራጃቸው እንዴት እንደሆነ ያሳያሉ።

ዋናው መሥሪያ ቤት—በተግባር የተደገፈ እምነት። ይህ አሳታፊ አውደ ርዕይ የበላይ አካሉ ኮሚቴዎች የሚሠሯቸውን ነገሮች ያብራራል፤ በተጨማሪም የበላይ አካሉ ኮሚቴዎች የይሖዋ ምሥክሮች አንድ ላይ እንዲሰበሰቡ፣ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ፣ መንፈሳዊ ምግብ እንዲመገቡና እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ የተሰጣቸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ትእዛዝ እንዲፈጽሙ የረዱት እንዴት እንደሆነ ያሳያል።

ያለአስጎብኚ የሚታይ ኤግዚቢሽን—ፓተርሰን

የመጀመሪያው መቶ ዘመን መንደር። ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበር መቃኘት ትፈልጋለህ? አንድን ጥንታዊ መንደር የሚያስቃኘው ይህ ኤግዚቢሽን በመጀመሪያው መቶ ዘመን የዕለት ተዕለት ሕይወት ምን እንደሚመስል የሚያስጎበኝ ብሎም የሚያሳትፍ አውደ ርዕይ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ ሕያው እንዲሆንልህ ያግዝሃል።

የመጀመሪያው መቶ ዘመን ሳንቲሞች። በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሱ የመጀመሪያው መቶ ዘመን ሳንቲሞች ለእይታ የቀረቡበት አውደ ርዕይ ነው። ስለ እያንዳንዱ ሳንቲም ትኩረት የሚስቡ ሐሳቦችን ታነብባለህ፤ ሳንቲሙ ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጋር ያለውን ግንኙነትም ትማራለህ።

“ልጆችሽም ሁሉ ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ።” ድርጅታችን ያዘጋጃቸውን ትምህርት ቤቶችና የሥልጠና ፕሮግራሞች የሚያስቃኝ አውደ ርዕይ ነው። ትምህርት ቤቶቹ፣ ራሳቸውን በፈቃደኝነት ያቀረቡ ተማሪዎች ውጤታማ አስተማሪ እና የጉባኤ ሽማግሌ እንዲሆኑ በማብቃት ረገድ ያበረከቱትን ድርሻ ትመለከታለህ።

‘ለምሥራቹ መሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ማድረግ።’ መራራ ተቃውሞ ቢገጥማቸውም እንኳ በእምነታቸው ለመደራደር ፈቃደኛ ያልሆኑ የይሖዋ ምሥክሮችን ቀልብ ሳቢ ታሪክ የሚያወሳ አውደ ርዕይ ነው። ድርጅታችን፣ የስብከቱ ሥራችን ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ ያከናወናቸውን ሥራዎችም ትጎበኛለህ።

 አድራሻ እና የስልክ ቁጥር

ዎርዊክ

አቅጣጫውን ለማግኘት

ፓተርሰን

አቅጣጫውን ለማግኘት

ዎልኪል

አቅጣጫውን ለማግኘት