በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 109

አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ

አጥብቃችሁ ከልብ ተዋደዱ

(1 ጴጥሮስ 1:22)

  1. 1. እውነተኛ ፍቅር ካለን

    አምላክን ’ናስደስታለን።

    እሱ ፍቅር ነው መለያው፤

    አፍቃሪ አምላክ ነው።

    ፍቅር ካለ በልባችን

    ያድጋል ወዳጅነታችን።

    ፍቅር ለኔ ብቻ የሚል፣

    ራስ ወዳድ አይደለም።

    ወዳጅነት ’ሚታየው

    በመከራ ጊዜም ጭምር ነው፤

    በችግር ጊዜ ስንደርስ፣

    ከጎናቸው ስንሆን ነው።

    ክርስቶስ ነው ምሳሌያችን፤

    ያባቱን ፍቅር አሳየን፤

    ስለ ፍቅር አስተማረን።

    እንምሰለው አምላክን

    በመዋደድ አጥብቀን።

(በተጨማሪም 1 ጴጥ. 2:17⁠፤ 3:8⁠፤ 4:8⁠ን እና 1 ዮሐ. 3:11⁠ን ተመልከት።)