በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የዎልኪል ፎቶ ጋለሪ 2 (ከኅዳር 2014 እስከ ኅዳር 2015)

የዎልኪል ፎቶ ጋለሪ 2 (ከኅዳር 2014 እስከ ኅዳር 2015)

የይሖዋ ምሥክሮች በዎልኪል፣ ኒው ዮርክ የሚገኘውን ቢሯቸውን የማስፋፋት ሥራ በቅርቡ አከናውነው ነበር። ይህ የፎቶ ጋለሪ ከኅዳር 2014 እስከ ኅዳር 2015 ባለው ጊዜ ውስጥ የተከናወነውን የግንባታ ሥራ ያሳያል።

በጥቅምት 15, 2015 ከአየር ላይ የተነሳ በዎልኪል የሚገኘውን ቢሮ የሚያሳይ ፎቶግራፍ።

  1. የማተሚያ ሕንፃ

  2. ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 1

  3. መኖሪያ ሕንፃ ሠ

  4. የመመገቢያ አዳራሽ

  5. የልብስ ማጠቢያ/ደረቅ እጥበት

  6. ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 2

  7. መኖሪያ ሕንፃ መ

ታኅሣሥ 4, 2014—ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 2

ለቢሮነት የሚያገለግለው አዲስ ሕንፃ መግቢያ ንጣፍ ለማንጠፍና አካባቢውን ለማሳመር ተዘጋጅቶ። በታች በኩል በስተ ግራ የሚታየው የእግረኛ መንገድ በክረምት ወቅት እግረኞችን እንዳያዳልጥ ሲባል ማሞቂያ ተገጥሞለታል። የቤቴል ቢሮ፣ የቅርንጫፍ ኮሚቴ ቢሮ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፍ የሚገኙት በዚህ ሕንፃ ውስጥ ነው።

ታኅሣሥ 5, 2014—መኖሪያ ሕንፃ መ

የሕንፃዎቹን የውስጥ ክፍሎች የሚሠራ አንድ ሰው የወለሉ ንጣፍ ከመገጠሙ በፊት ግራይንደር ተጠቅሞ ወለሉን ሲያስተካክል። ግራይንደሩ አቧራ ስቦ ከሚያጸዳ ቫኪዩም ጋር ተያይዟል።

ጥር 9, 2015—መኖሪያ ሕንፃ ሠ

በመኖሪያ ሕንፃ ሠ የሚኖሩት ከ200 በላይ የሚሆኑ ቤቴላውያንና ሌሎች ጎብኚዎች አረፍ ብለው የሚጨዋወቱበት ቦታ ታድሷል። በዚህ ሕንፃ ላይ ከተደረገው እድሳት መካከል ኃይል ቆጣቢ የሆኑ መስኮቶችና እሳት ሲነሳ የሚጮኽ አዲስ ደወል መግጠም ይገኝበታል።

የካቲት 9, 2015—የማተሚያ ሕንፃ

አንድ የቴክኒክ ባለሙያ የቴክኒክ ሥልጠና በሚሰጥበት ክፍል ውስጥ ገመድ ሲቀጥል። ይህ ክፍል የተዘጋጀው የቧንቧ ሥራን፣ የኤሌክትሪክ ጥገናን፣ የደህንነት መመሪያዎችንና እነዚህ የመሳሰሉ ጉዳዮችን አስመልክቶ ሥልጠና ለመስጠት ነው።

የካቲት 17, 2015—የማተሚያ ሕንፃ

አንዲት የኤሌክትሪክ ባለሙያ የቴክኒክ ሥልጠና ለሚሰጥበት አዲስ ክፍል መብራት ስትገጥም።

መጋቢት 2, 2015—ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 1

አንዲት ሠራተኛ የኤሌክትሪክ ሽቦ በያዙት ቱቦዎች መካከል ያለውን ክፍተት ስትለካ። ይህ ቦታ የታደሰው በብሩክሊን የነበሩት የቅርንጫፍ ቢሮ ዲፓርትመንቶች እንዲጠቀሙበት ነው።

መጋቢት 3, 2015—መኖሪያ ሕንፃ መ

አንድ የቧንቧ ሠራተኛ ሙቅ ውኃ የሚሄድባቸውን ቧንቧዎች ሲሠራ።

መጋቢት 31, 2015—መኖሪያ ሕንፃ መ

የሕንፃውን የውጭ ክፍል የሚሠሩ ሰዎች በማንሻ መሣሪያ ላይ ሆነው በመስኮት ጠርዝ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ሲደፍኑ። በዚህ ሕንፃ ላይ ብቻ 298 እንደዚህ ያሉ ኃይል ቆጣቢ መስኮቶች አሉ፤ እነዚህ መስኮቶች ሕንፃውን ለማሞቅና ለማቀዝቀዝ የሚወጣውን ኃይል ለመቀነስ ይረዳሉ።

ሚያዝያ 17, 2015—ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 1

ግንበኞች በ1970ዎቹ በተሠራው ግንብ ላይ የነበሩ ድንጋዮችን በመጠቀም በመካከለኛው የመኪና ማቆሚያ ያለውን ግንብ በድጋሚ ሲሠሩ። የመኪና ማቆሚያው የሚገኘው ለቢሮነት በሚያገለግለው ሕንፃ 1 እና በመኖሪያ ሕንፃ ሠ መካከል ነው።

ሚያዝያ 17, 2015—ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 1

አንድ ሠራተኛ ግድግዳው ቀለም ከመቀባቱ በፊት በብርጭቆ ወረቀት ሲያለሰልሰው። የሒሳብ፣ የኮምፒውተርና የዕቃ ግዢ ክፍሎች በዚህ ሕንፃ ውስጥ ይገኛሉ።

ሰኔ 8, 2015—መኖሪያ ሕንፃ መ

አንድ የኤሌክትሪክ ባለሙያ የኤሌክትሪክ ሽቦን ከመብረቅ መከላከያው ጋር ለማገናኘት ሽቦውን ወደ ጣሪያው ሲጎትት። መብረቅ ሲጥል መከላከያው ከመብረቁ የመጣውን የኤሌክትሪክ ኃይል ተቀብሎ ወደ መሬት በማስተላለፍ ሕንፃው ጉዳት እንዳይደርስበት ይከላከላል።

ሰኔ 8, 2015—መኖሪያ ሕንፃ መ

በዎልኪል የቢሮ ማስፋፊያ ፕሮጀክቱ በሚከናወንበት ወቅት በፎቶግራፉ ላይ የሚታዩትን ዛፎች ጨምሮ ቀድሞ የነበረው የግቢው ገጽታ እንዳይቀየር ለማድረግ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል። በስተ ግራ በኩል የሚታየው የውኃ ታንከር 150,000 ሊትር ውኃ የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን በዎልኪል ቢሮ ለሚኖረው የውኃ አቅርቦት እንዲሁም የእሳት አደጋን መከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ሰኔ 25, 2015—ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 1

አንድ የእንጨት ባለሙያ በስብሰባ አዳራሹ የኋላ ግድግዳ ላይ የተቆራረጡ እንጨቶች ሲደረድር፤ በዚህ ግድግዳ ላይ 1,800 የእንጨት ቁርጥራጮች ይደረደራሉ። የተለያየ ውፍረት ያላቸው እነዚህ የእንጨት ቁርጥራጮች ድምፅ በጣም እንዳያስተጋባ ለማድረግ ይረዳሉ።

ሐምሌ 9, 2015—ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 2

ቻርልስ ሪድ ከ1958 ጀምሮ በቤቴል አገልግሏል። ወንድም ሪድ፣ በዩናይትድ ስቴትስና በሌሎች አገሮች የሚሰራጩት ጽሑፎች በብሩክሊን ቤቴል ይታተሙ በነበረበት ወቅት ለማተሚያ መሣሪያው የሚያገለግሉ ኮንክሪት ፓዶችን ንድፍ በማውጣትና በመግጠሙ ሥራ ተካፍሏል። ወንድም ሪድ በዎልኪል የሚገኘው ቢሮ የማስፋፊያ ሥራ ሲካሄድ የጥራት ተቆጣጣሪ ሆኖ አገልግሏል።

ነሐሴ 17, 2015—ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 1

ሠራተኞች ለስብሰባ አዳራሹ የሚያገለግሉ አዳዲስ ወንበሮችን ሲያወርዱ። የታደሰው አዳራሽ 812 ሰዎችን መያዝ የመያዝ አቅም አለው።

መስከረም 21, 2015—ለቢሮነት የሚያገለግል ሕንፃ 1

በአዳራሹ ላይ የተደረገው እድሳት የቪዲዮ ማሳያ ስክሪኖችን መግጠምንና ጣሪያው ድምፅ ውጦ የሚያስቀር እንዲሆን ማድረግን ይጨምራል።

ጥቅምት 12, 2015—መኖሪያ ሕንፃ መ

በታደሰው ክሊኒክ ውስጥ የነርሶች ክፍል ሲዘጋጅ። ለሕመምተኞች አመቺ እንዲሆን ሲባል ኮሪደሮቹና መታጠቢያ ክፍሎቹ እንዲሰፉ ተደርጓል።

ጥቅምት 15, 2015—የዎልኪል የግንባታ ቦታ

ወደ 2,000 የሚጠጉ የቤቴል ቤተሰብ አባላት የሚኖሩበት በዎልኪል የሚገኘው ቢሮ ከአየር ላይ ሲታይ። በድምሩ 102,000 ካሬ ሜትር የሚያክል ስፋት ያላቸውን ሕንፃዎች መገንባትና ማደስን የሚያጠቃልለው የዎልኪል ቢሮ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ኅዳር 30, 2015 ተጠናቋል።