በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል ማን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል ማን ነው?

 ጥቂት ቁጥር ያላቸው የጎለመሱ ክርስቲያኖችን ያቀፈው የበላይ አካል በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች መመሪያ ይሰጣል። እነዚህ ክርስቲያኖች ድርብ ሥራ ያከናውናሉ፦

 የበላይ አካሉ፣ በመጀመሪያ መቶ ዘመን ጠቅላላውን የክርስቲያን ጉባኤ የሚመለከቱ ትላልቅ ውሳኔዎች ያስተላለፉትን በኢየሩሳሌም ይገኙ የነበሩ “ሐዋርያትና ሽማግሌዎች” ምሳሌ ይከተላል። (የሐዋርያት ሥራ 15:2) እንደነዚህ ታማኝ ወንዶች ሁሉ የበላይ አካል አባላትም የድርጅታችን መሪዎች አይደሉም። የበላይ አካሉ አባላት የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያ ይከተላሉ፤ እንዲህ ማድረጋቸው ይሖዋ አምላክ የጉባኤው ራስ አድርጎ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሾመው አምነው እንደተቀበሉ ያሳያል።—1 ቆሮንቶስ 11:3ኤፌሶን 5:23

የበላይ አካል አባላት እነማን ናቸው?

 የበላይ አካል አባላት ኬነዝ ኩክጌጅ ፍሊግልሳሙኤል ኸርድጄፍሪ ጃክሰንስቲቨን ሌትጌሪት ሎሽማርክ ሳንደርሰንዴቪድ ስፕሌን እና ጄፍሪ ዊንደር ናቸው። እነዚህ ወንድሞች ዎርዊክ፣ ኒው ዮርክ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ያገለግላሉ።

የበላይ አካሉ የተዋቀረው እንዴት ነው?

 የበላይ አካሉ የሥራችንን የተለያዩ ገጽታዎች በበላይነት ለመከታተል በስድስት ኮሚቴዎች የተዋቀረ ሲሆን እያንዳንዱ የበላይ አካል አባል በአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ኮሚቴዎች ውስጥ ያገለግላል።

  •   የአስተባባሪዎች ኮሚቴ፦ በዚህ ኮሚቴ ውስጥ የሚያገለግሉት ወንድሞች ሕግ ነክ ጉዳዮችን ይከታተላሉ፤ በተጨማሪም አደጋ ሲከሰት፣ በሃይማኖታዊ አቋማቸው የተነሳ በእምነት ባልንጀሮቻችን ላይ ስደት ሲደርስ እንዲሁም የይሖዋ ምሥክሮችን የሚነኩ ሌሎች አጣዳፊ ነገሮች ሲያጋጥሙ አስፈላጊውን እርዳታ ይሰጣሉ።

  •   የፐርሶኔል ኮሚቴ፦ ለቤቴል ቤተሰብ አባላት የተደረጉ ዝግጅቶችን በበላይነት ይከታተላል።

  •   የሕትመት ኮሚቴ፦ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን የማተሙንና የማሰራጨቱን ሂደት እንዲሁም የስብሰባ አዳራሾችን፣ የትርጉም ቢሮዎችንና የቅርንጫፍ ቢሮዎችን ግንባታ ይከታተላል።

  •   የአገልግሎት ኮሚቴ፦ ‘የመንግሥቱን ምሥራች’ የመስበኩን ሥራ በበላይነት ይከታተላል።—ማቴዎስ 24:14

  •   የትምህርት ኮሚቴ፦ በስብሰባዎች፣ በትምህርት ቤቶች፣ በድምፅና በቪዲዮ ፕሮግራሞች አማካኝነት የሚዘጋጁ መንፈሳዊ ትምህርቶችን በበላይነት ይከታተላል።

  •   የጽሑፍ ዝግጅት ኮሚቴ፦ በጽሑፍ የሚታተሙትንም ሆነ በድረ ገጻችን ላይ የሚወጡትን መንፈሳዊ ትምህርቶች እንዲሁም የትርጉም ሥራውን በበላይነት ይከታተላል።

 የበላይ አካሉ አባላት በእነዚህ ኮሚቴዎች ውስጥ ከሚያከናውኗቸው ተግባራት በተጨማሪ ከድርጅቱ ሥራ ጋር በተያያዘ አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ላይ ለመወያየት በየሳምንቱ ይሰበሰባሉ። በዚህ ስብሰባ ላይ የሚነሱትን ጉዳዮች በተመለከተ ቅዱሳን መጻሕፍት ምን እንደሚሉ ይወያያሉ፤ የአምላክን ቅዱስ መንፈስ አመራር ይከተላሉ፤ እንዲሁም በአንድ ልብ ለመወሰን ጥረት ያደርጋሉ።—የሐዋርያት ሥራ 15:25

የበላይ አካሉ ረዳቶች እነማን ናቸው?

 እነዚህ ወንድሞች የበላይ አካሉን ኮሚቴዎች የሚረዱ እምነት የሚጣልባቸው ክርስቲያኖች ናቸው። (1 ቆሮንቶስ 4:2) የተመደቡበት ኮሚቴ ከሚያከናውነው ሥራ ጋር በተያያዘ ጥሩ ችሎታና ተሞክሮ ያላቸው ሲሆን ኮሚቴው በሚያደርገው ሳምንታዊ ስብሰባ ላይ ይገኛሉ። ረዳቶቹ ውሳኔ በማድረጉ ሥራ ባይካፈሉም ጥሩ ሐሳብ ይሰጣሉ፤ ስለ አንድ ጉዳይ ዝርዝር መረጃ ያቀርባሉ፤ ኮሚቴው የሚያስተላልፈው ውሳኔ እንዲፈጸም ያደርጋሉ፤ ብሎም የአፈጻጸሙን ሂደትና ውጤቱን ይከታተላሉ። በተጨማሪም የበላይ አካሉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ወንድሞችን እንዲጎበኙ ወይም እንደ ዓመታዊ ስብሰባ ወይም የጊልያድ ምረቃ ባሉ ፕሮግራሞች ላይ ክፍል እንዲያቀርቡ ሊመድባቸው ይችላል።

የረዳቶች ስም ዝርዝር

ኮሚቴ

ስም

የአስተባባሪዎች

  • ጆን ኤክረን

  • ፖል ጊሊስ

  • ትሮይ ስናይደር

የፐርሶኔል

  • ጄራልድ ግሪዝል

  • ፓትሪክ ለፍራንከ

  • ዳንኤል ሞልቸን

  • ማርክ ስኮት

  • ራልፍ ዎልስ

የሕትመት

  • ሮበርት በትለር

  • ሃሮልድ ኮርከርን

  • ጋይዩስ ግሎከንቲን

  • ዶናልድ ጎርደን

  • ሮበርት ሉሲዮኒ

  • አሌክስ ራይንሙለር

  • ዴቪድ ሲንክሌር

የአገልግሎት

  • ጌሪ ብሮ

  • ጆኤል ዴሊንገር

  • ቤቲ ጆርጅስ

  • አንቶኒ ግሪፍን

  • ሴት ሃያት

  • ጆዲ ጄድሊ

  • ክሪስቶፈር ሜቨር

  • ባልታሳር ፔርላ

  • ጄከብ ረምፍ

  • ጆናታን ስሚዝ

  • ዊልያም ተርነር

  • ሊዮን ዊቨር

የትምህርት

  • ማይክል ባንክስ

  • ሮናልድ ከርዛን

  • ኬነዝ ፍሎዲን

  • ዊልያም ማለንፎንት

  • ማርክ ኑሜር

  • ዴቪድ ሼፈር

የጽሑፍ

  • ኒኮላስ አላዲስ

  • ፒር ክሪስተንሰን

  • ሮበርት ሲራንኮ

  • ኬነዝ ጎድበርን

  • ጄምስ ማንትስ

  • ኢሳክ መሬ

  • ክላይቭ ማርቲን

  • ሌናርድ ማየርስ

  • ጂን ስሞሊ

  • ኸርማነስ ቫን ዘልም