በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሁለተኛ ሳሙኤል መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • ዳዊት፣ ሳኦል መሞቱን ሰማ (1-16)

    • ዳዊት ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን የተቀኘው የሐዘን እንጉርጉሮ (17-27)

  • 2

    • ዳዊት በይሁዳ ላይ ነገሠ (1-7)

    • ኢያቡስቴ በእስራኤል ላይ ነገሠ (8-11)

    • በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል ውጊያ ተካሄደ (12-32)

  • 3

    • የዳዊት ቤት እየበረታ ሄደ (1)

    • የዳዊት ወንዶች ልጆች (2-5)

    • አበኔር ለዳዊት ወገነ (6-21)

    • ኢዮዓብ አበኔርን ገደለው (22-30)

    • ዳዊት ለአበኔር የሐዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ (31-39)

  • 4

    • ኢያቡስቴ ተገደለ (1-8)

    • ዳዊት የኢያቡስቴን ገዳዮች አስገደላቸው (9-12)

  • 5

    • ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ (1-5)

    • ኢየሩሳሌም ተያዘች (6-16)

      • የዳዊት ከተማ ተብላ የምትጠራው ጽዮን (7)

    • ዳዊት ፍልስጤማውያንን ድል አደረገ (17-25)

  • 6

    • ታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ (1-23)

      • ዖዛ ታቦቱን በመያዙ ተቀሰፈ (6-8)

      • ሜልኮል ዳዊትን ናቀችው (16, 20-23)

  • 7

    • ዳዊት ቤተ መቅደሱን እንደማይሠራ ተነገረው (1-7)

    • ለዳዊት የመንግሥት ቃል ኪዳን ተገባለት (8-17)

    • ዳዊት ያቀረበው የምስጋና ጸሎት (18-29)

  • 8

    • ዳዊት የተቀዳጃቸው ድሎች (1-14)

    • የዳዊት አስተዳደር (15-18)

  • 9

    • ዳዊት ለሜፊቦስቴ ታማኝ ፍቅር አሳየው (1-13)

  • 10

    • በአሞናውያንና በሶርያውያን ላይ የተገኘ ድል (1-19)

  • 11

    • ዳዊት ከቤርሳቤህ ጋር ምንዝር ፈጸመ (1-13)

    • ዳዊት ኦርዮን ለማስገደል ሁኔታውን አመቻቸ (14-25)

    • ዳዊት ቤርሳቤህን አገባ (26, 27)

  • 12

    • ናታን ዳዊትን ገሠጸው (1-15ሀ)

    • የቤርሳቤህ ልጅ ሞተ (15ለ-23)

    • ቤርሳቤህ ሰለሞንን ወለደች (24, 25)

    • የአሞናውያን ከተማ የሆነችው ራባ ተያዘች (26-31)

  • 13

    • አምኖን ትዕማርን አስነወራት (1-22)

    • አቢሴሎም አምኖንን ገደለው (23-33)

    • አቢሴሎም ወደ ገሹር ሸሸ (34-39)

  • 14

    • ኢዮዓብና ተቆአዊቷ ሴት (1-17)

    • ዳዊት ተቆአዊቷን ሴት የላካት ኢዮዓብ መሆኑን ደረሰበት (18-20)

    • አቢሴሎም ወደ ቤቱ እንዲመለስ ተፈቀደለት (21-33)

  • 15

    • የአቢሴሎም ሴራና ዓመፅ (1-12)

    • ዳዊት ከኢየሩሳሌም ሸሸ (13-30)

    • አኪጦፌል ከአቢሴሎም ጋር አበረ (31)

    • ኩሲ የአኪጦፌልን ምክር ውድቅ እንዲያደርግ ተላከ (32-37)

  • 16

    • ሲባ የሜፊቦስቴን ስም አጠፋ (1-4)

    • ሺምአይ ዳዊትን ረገመው (5-14)

    • አቢሴሎም ኩሲን ተቀበለው (15-19)

    • የአኪጦፌል ምክር (20-23)

  • 17

    • ኩሲ የአኪጦፌልን ምክር ውድቅ አደረገ (1-14)

    • ዳዊት እንዲጠነቀቅ ተነገረው፤ ከአቢሴሎም አመለጠ (15-29)

      • ቤርዜሊና አብረውት ያሉት ሰዎች ለንጉሡ ስንቅ አቀበሉ (27-29)

  • 18

    • አቢሴሎም ለሽንፈትና ለሞት ተዳረገ (1-18)

    • ዳዊት፣ አቢሴሎም መሞቱ ተነገረው (19-33)

  • 19

    • ዳዊት ለአቢሴሎም አለቀሰ (1-4)

    • ኢዮዓብ ዳዊትን ገሠጸው (5-8ሀ)

    • ዳዊት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ (8ለ-15)

    • ሺምአይ ይቅርታ ጠየቀ (16-23)

    • ሜፊቦስቴ በዳዊት ላይ የፈጸመው በደል እንደሌለ ተረጋገጠ (24-30)

    • ቤርዜሊ የንጉሡን አክብሮት አተረፈ (31-40)

    • በእስራኤልና በይሁዳ ሰዎች መካከል ውዝግብ ተፈጠረ (41-43)

  • 20

    • ሳባ ዓመፀ፤ ኢዮዓብ አሜሳይን ገደለው (1-13)

    • ሳባን አሳደው ደረሱበት፤ እንዲሁም ተገደለ (14-22)

    • የዳዊት አስተዳደር (23-26)

  • 21

    • ገባኦናውያን የሳኦልን ቤት ተበቀሉ (1-14)

    • ከፍልስጤማውያን ጋር የተደረጉ ጦርነቶች (15-22)

  • 22

    • ዳዊት፣ ይሖዋ ከጠላቶቹ ስለታደገው ውዳሴ አቀረበ (1-51)

      • “ይሖዋ ቋጥኜ፣ ምሽጌና ታዳጊዬ ነው” (2)

      • ይሖዋ ታማኝ ለሆነ ሰው ታማኝ ይሆናል (26)

  • 23

    • የዳዊት የመጨረሻ ቃላት (1-7)

    • የዳዊት ኃያላን ተዋጊዎች የፈጸሙት ጀብዱ (8-39)

  • 24

    • ዳዊት ሕዝቡን በመቁጠር የፈጸመው ኃጢአት (1-14)

    • ይሖዋ በላከው ቸነፈር 70,000 ሰዎች ሞቱ (15-17)

    • ዳዊት መሠዊያ ሠራ (18-25)

      • ‘ምንም ያልከፈልኩበትን ነገር መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም’ (24)