በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ፖርኖግራፊ መመልከት ሱስ ከሆነብኝ ምን ላድርግ?

ፖርኖግራፊ መመልከት ሱስ ከሆነብኝ ምን ላድርግ?

ምን ማድረግ ትችላለህ?

 ፖርኖግራፊ ርካሽ ነገር መሆኑን ተገንዘብ። ፖርኖግራፊ አምላክ ክቡር አድርጎ የፈጠረውን ነገር ለማራከስ የሚያገለግል መሣሪያ መሆኑ ግልጽ ነው። ሁኔታውን ከዚህ አንጻር መመልከትህ ’ክፋትን እንድትጠላ’ ይረዳሃል።—መዝሙር 97:10

 የሚያስከትላቸውን መዘዞች አስብ። ፖርኖግራፊ በምስሉ ላይ የሚታዩትን ሰዎች ክብር ያዋርዳል። የሚመለከተውንም ሰው ክብር ይቀንሳል። መጽሐፍ ቅዱስ “አስተዋይ ሰው አደጋ ሲያይ መጠጊያ ይሻል” ማለቱ የተገባ ነው።—ምሳሌ 22:3

 ለራስህ ቃል ግባ። ታማኝ የነበረው ኢዮብ “ቆንጆይቱን በፍትወት ዐይን እንዳልመለከት፥ ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቼአለሁ” ሲል ተናግሯል። (ኢዮብ 31:1 የታረመው የ1980 ትርጉም) አንተም እንደሚከተለው እያልክ ለራስህ ‘ቃል መግባት’ ትችላለህ፦

  •  ቤት ውስጥ ብቻዬን ከሆንኩ ኢንተርኔት አልጠቀምም።

  •  ፖርኖግራፊ የያዙ ድረ ገጾች ካጋጠሙኝ ወይም እንዲህ ያሉ ምስሎችን እንድመለከት የሚጋብዙ መልእክቶች ከመጡ ወዲያውኑ አጠፋቸዋለሁ።

  •  ችግሩ ካገረሸብኝ ጉዳዩን ጎልማሳ ለሆነ አንድ የምቀርበው ሰው አጫውተዋለሁ።

ክር እጅህ ላይ በተተበተበ ቁጥር ማላቀቁ ከባድ እንደሚሆን ሁሉ ፖርኖግራፊ ደጋግመህ በተመለከትክ ቁጥርም ልማዱ ይበልጥ ተብትቦ ይይዝሃል

 ጉዳዩን አስመልክተህ ጸልይ። መዝሙራዊው “ከንቱ ነገር ከማየት ዐይኖቼን መልስ” በማለት ወደ ይሖዋ ጸልዮአል። (መዝሙር 119:37) አምላክ ይህን ችግር እንድታሸንፍ ይፈልጋል፤ ስለዚህ ስለ ጉዳዩ ወደ እሱ ከጸለይክ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ የሚያስፈልግህን ጥንካሬ ይሰጥሃል!—ፊልጵስዩስ 4:13

 አንድ ሰው አማክር። ለምትተማመንበት አንድ ሰው ችግርህን ማማከርህ ብዙውን ጊዜ ይህን ልማድ ለማሸነፍ የሚረዳህ ወሳኝ እርምጃ ነው።—ምሳሌ 17:17

 ልታስታውሰው የሚገባ ነገር፦ ፖርኖግራፊ ለመመልከት የሚያጋጥምህን ፈተና ባለፍክ ቁጥር ከፍተኛ ድል እንዳገኘህ ሊሰማህ ይገባል። ፈተናውን ባለፍክ ቁጥር ስለ ሁኔታው ወደ ይሖዋ በመጸለይ ጥንካሬ ስለሰጠህ አመስግነው። ከፖርኖግራፊ ስትርቅ የይሖዋን ልብ ደስ ታሰኛለህ!—ምሳሌ 27:11